Ethio Compass

Ethio Compass Jesus is the only way of heaven

05/06/2025

ጌታዬ ባንት ሰው ሆኛለውና
እስኪ ልሰዋልህ ክብር ምስጋና
እምባዬን ጠርገህ ማቄን ቀደሃል
ሃዘን ምሬቴን ከኔ ወስደሃል

እነዚ ሰዎች ምንድነው ሚያጨሱት
17/01/2025

እነዚ ሰዎች ምንድነው ሚያጨሱት

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የዋጋ ንረት ከ30 በመቶ ወደ 17 በመቶ ዝቅ እንዲል አግዟል - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የዋጋ ንረት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 17 በመቶ ዝቅ እንዲል አግዟል ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ በጥብቅ ዲሲፒሊን እየተመራ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ውጤት እያስገኘ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ለአብነትም የብር ምንዛሪ ዋጋ በገበያ እንዲወሰን በመደረጉ ወርቅ አምራቶች ምርታቸውን በማዕከላዊ ገበያ ለብሔራዊ ባንክ እንዲሸጡ አነሳስቷቸዋል ብለዋል፡፡

ማሻሻያው ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የሚያመርቱ ድርጅቶችን እያጠናከራቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት፣ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለሸቀጦት ዋጋ መረጋጋትም ከፍተኛ ጠቀሜታ እያስገኘ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ተግበራዊ የተደረገው የገንዘብ ፖሊሲ መንግስት ከግምጃ ቤት የሚበደረውን የገንዘብ መጠን እንዲገደብ እና ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን በ18 በመቶ ብቻ እንዲያድግ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡

ይህም ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር የተመጣጠነ የገንዘብ አቅርቦት እና ፍሰት በገበያ ውስጥ እንዲኖር በማስቻል የዋጋ መረጋጋት እንዲኖር እና አምራቾች እንዲበረታቱ በማድረግ ውጤታማ ሊሆን መቻሉን አብራርተዋል።

የገንዘብ ፖሊሲው መተግበር የዋጋ ንረት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 17 በመቶ ዝቅ እንዲል እገዛ ማድረጉንም አንስተው፤ ማሻሻያው የባንኮች ቁጠባ እንዲያድግ እና ለኢኮኖሚ የሚያቀርቡት ብድር እየተጠናከር እንዲሄድ ማስቻሉን አስረድተዋል፡፡

የዋጋ ንረቱ ከነበረበት ዝቅ ብሏል ማለት የሸቀጦች ዋጋ አልጨመረም ማለት አይደለም፤ የኑሮ ውድነትን ቀንሷል ማለት እንዳልሆነም አብራርተዋል፡፡

በአንጻሩ የዋጋ ንረቱ ከነበረበት ዝቅ ብሏል ማለት የሸቀጦች ዋጋ በየአመቱ ያድግ ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 17 በመቶ ዝቅ ብሎ እንዲያድግ ረድቷል ማለት ነው ብለዋል፡፡

የሸቀጦችን የዋጋ እድገት መቼም ቢሆን ማቆም አይቻልም፤ ይህ ከሆነ እድገት ይቆማል ወይም ይገታል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ይልቁንስ እድገቱ ጤናማ እንዲሆን ማድረግ ነው የሚቻለው ያሉት ሚኒስትሩ÷ ለዚህም የዋጋ ጭማሪው ከሁለት አሃዝ በታች እንዲሆን ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

የዋጋ ንረትን በዘላቂነት ለመከላከልም በገበያ ውሥጥ በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መንግስት ለስትራቴጂክ እና መሰረታዊ ሸቀጦች በተለይም ለማዳበሪያ፣ ለነዳጅ፣ ለዘይት፣ ለመድሃኒትና ለመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ ድጎማና ለሌሎች ከ400 ቢሊየን ብር በላይ ድጎማ እያደረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመስኖ ልማት ብቻ እስካሁን 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ሄክታር በዘር መሸፈኑን ጠቁመው÷ ይህም ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የነደፈችውን ትልም ለማሳካት መሰረት እንደሚጥል ይታመናል ብለዋል፡፡

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተጀመሩ የሌማት ትሩፋት እና የግብርና ስራዎች የበጋ ወቅት ርብርብ ማዕከል ሆነው መቀጠላቸውን ተናግረዋል፡፡

በሚቀጠሉት ሁለት ዓመታት ኢትዮጵያን ከተረጂነት እና ጠባቂነት የሚያላቅቁ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ለመጪው የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ እና ሌሎች ኮንፈረንሶች አስፈላጊው ዘርፈ ብዙ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

ሰበር - ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰማ።  የአሜሪካ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ካልተሸጠ በጃንዋሪ 19 2025 እ. ኤ.አ እንዲዘጋ...
17/01/2025

ሰበር - ሲጠበቅ የነበረው የፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰማ። የአሜሪካ ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት ቲክቶክ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ካልተሸጠ በጃንዋሪ 19 2025 እ. ኤ.አ እንዲዘጋ በስር ፍርድ ቤቶች የተወሰነውን ውሳኔ ያለተቃውሞ በሙሉ ድምጽ ደግፎታል።
ፍርድ ቤቱ በውሳኔው "ቲክቶክ ከ170 ሚልየን ተጠቃሚዎቹ የመናገር ነጻነት አንጻር፣ ከቻይና መንግስትጋ ያለው ቁርኝት ለአገር ደህንነት አስጊ እንደሆነና ይህን ተከትሎም የግድ ለአሜሪካ ባለሀብቶች ተሸጦ በአሜሪካ ህግ እንዲዋቀር" ሲል ሃሳብ ሰጥቷል።

20/02/2023
ውድ ደንበኞቻችን በጥራታቸው ልዩ የሆኑትን የ Bakemate ተወዳጅ ምርቶቻችንን ማለትምCream shantille 1kg and 10kgCusturd 1kg and 10kg Super Gato 1kg a...
03/12/2022

ውድ ደንበኞቻችን በጥራታቸው ልዩ የሆኑትን የ Bakemate ተወዳጅ ምርቶቻችንን ማለትም
Cream shantille 1kg and 10kg
Custurd 1kg and 10kg
Super Gato 1kg and 10kg
Liquid Glucose 5kg
Gelatine Powder 70g and 700gm
Corn Starch Natural 25 kg
Cocoa Powder 25kg
Extra virgine olive oil speroni tin 5Ltr
Bakemate Yeast 450g
Ice Cream mix vanilla 1kg and 5kg
Ice Cream mix Chocolate 1kg and 5kg
Neovanilla powder 250g
Dates Dough 1kg እና የተለያዩ ቱልሶችንም ያስገባን መሆኑን
እየገለፅን፣ምርቶቻችንን በሁሉም የመሸጫ ሱቆቻችን ያገኛሉ::
አድራሻችን፡- መገናኛ አደባባይ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ አማረ አብራሀምና ቤተሰቦቹ ህንፃ
ስልክ፡-0993822421
ጀሞ ሚካኤል አፍሪካ ህንፃ በሮዛ ዳቦ ቤት 100 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡- 0935986904
ቤተል ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 0965211897

Address

Addis Ababa
Woliso

Telephone

+251929413278

Website

http://danobjmak.com/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Compass posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Compass:

Share