06/06/2026
የምስጋና መልዕክት
ከተርሂም የምግብ ምርቶች ኃ.የተ.የግ.ማህበር
ሰሞኑን በማምረቻችን አጋጥሞን በነበረው የናፍጣ አቅርቦት ችግር ምክንያት ያቀረብነውን ጥያቄ ተቀብለው፣ ችግራችንን ከልብ ተረድተው አፋጣኝ መፍትሄ ለሰጡን የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በውይይታችን ወቅት በነበሩብን የኮሚኒኬሽን (የመረጃ ልውውጥ) ክፍተቶች ላይ በግልጽ ተነጋግረን መግባባት ላይ የደረስን ሲሆን፣ የሚመለከታቸው ኃላፊዎችም ይህንን የነዳጅ አቅርቦት ችግር በቀጣይነት እና በዘላቂነት ለመፍታት የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ አረጋግጠውልናል።
እኛም በበኩላችን ከተቋማቱ የተሰጡንን ገንቢ አስተያየቶች እና አቅጣጫዎች በሙሉ ልብ ተቀብለን፣ አሰራራችንን ለማስተካከል የተቻለንን ሁሉ ጥረት እናደርጋለን። በቀጣይም ምንም አይነት የምርት መቆራረጥ እንዳይኖር እና ለህዝባችን የምናቀርበውን የዳቦ ምርት ያለምንም መስተጓጎል ለማቅረብ ጠንክረን እንደምንሰራ ለደንበኞቻችን እና ለማህበረሰቡ ልናረጋግጥ እንወዳለን።
ስላደረጋችሁልን ትብብር እና ላሳያችሁን አጋርነት በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን!